በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር የኦዲት አገልግሎት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መጋረጃ እና ጄኔሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒዮ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመግዛት ጠቅላላ ዋጋ /ታክሱን ጨምሮ/ በመሙላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት 10 በመቶ ውል ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0934879762 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዊ ልማት ማህበር