ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
14

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት እስከ ሰኔ 30 ድረስ ለሆስፒታሉ ለኦክስጂን፣ መድሃኒትና የህክምና መሳሪያ መጫኛ አገልግሎት የሚውል አይሱዚ የጭነት መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዓ/ህግ ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. መኪናው የሚፈልጋቸውን ወጭዎች ከናፍጣ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ባለንብረቱ (ባለሃብቱ) የሚሸፍን፡፡
  5. ከነሀሴ 26/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ውል ሊወስድ የሚችል፡፡
  6. የመኪና ሊብሪ ያላቸው ሆኖ ሆስፒታሉ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን ተወዳዳሪ አሸናፊ አድርጎ የሚለይ ይሆናል፡፡
  7. መኪናው አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ወይም ጊዜ ሲደወልለት መቅረብ የሚችል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የሳንጃ የመጀመሪያ ደርጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፤ ጨረታው ከወጣበት ከነሀሴ 26/2017 እስከ መስከረም 05/2018 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  10. የጨረታው ሳጥን የሚታሽገው 05/01/2018 ዓ.ም 11፡30 ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዳራሽ 06/01/ 2018 ከጠዋቱ 3፡00 ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩ ብር አንድ በመቶ ጠቅላላ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጀናልና ኮፒውን በተለያየ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. አሸናፊ ድርጀት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ብሩን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here