የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ አስተዳደር ስር ላሉ ተሽከርካሪዎች እና በዞኑ ስር ላሉ 7 ወረዳዎች እንዲሁም ለ3 ከተማ አስተዳደር ለ2017 በጀት ዓመት ለአንድ ዓመት የሚቆይ የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላችሁ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ጎጃም ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ /የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት አምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ መፈረም አለበት። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ቢሮው ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 7,000 /ሰባት ሽህ ብር/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ፤ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ክብረ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 መቀመጫዉን ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 16 የተባበሩት ማደያ ጀርባ የአማራ ህንጻ ዲዛይን ከተከራየዉ ቢሮ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ ዘግይቶ ለቢሮአችን ቢደርስ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በጨረታው ተሳታፊ የሚሆኑ የንግድ ድርጅቶች የእጅ ዋጋ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡበት ቦታ ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዉስጥ መሆን አለባቸው፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ