ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
26

የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/02/2017

በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን /ፑል/፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጨምሮ ለ2ቱም መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት በመ/ቤቱ የሚገኙ ቀላል ተሽከርካሪዎችን በ2ኛና በ3ኛ ደረጃ በግል ጋራዥ በዓመታዊ ኮንትራት ለማስጠገን በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በመ/ቤቱ የሚገኙ ቀላል ተሽከርካሪዎችን በ2ኛና በ3ኛ ደረጃ በግል ጋራዥ በአመታዊ ኮንትራት ውል በመያዝ ለማሰራት የሚሣተፋ በባህርዳር ከተማ ጋራዥ ቦታ ያላቸው መኖሩን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላችሁ ፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1 – 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  5. የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይቻላል ፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን አስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በ8.00 ሰዓት ተዘግቶ በ8.30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44/058 220 96 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን /ፑል/

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here