በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2017 በጀት ዓመት ለሚገነባው የከሚሴ እናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የሚውል ሎት 1. የአልሙኒየም ገጠማ ሥራ፣ ሎት 2. ሴራሚክና ፎርስሊን ንጣፍ አቅርቦት እና ሎት 3. ማርብልና ግራናይት ንጣፍ ሥራ አቅርቦት በዘርፉ በተሰማሩ ሕጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቹ በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ዋና /ኦርጅናል/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም የተከለከለ ነው፤ ተቀባይነትም የለውም፡፡
3. ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ወልዲያ ከተማ ጎማጣ በሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን 11:00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫታቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
4. ክፍያን በተመለከተ በሁሉም ሎቶች በአማካሪዎች የጸደቀ በማቅረብና በጸደቀ ሳምፕል መሰረት ቦታው ድረስ ማቅረብ ሲችሉ ነው፡፡
5. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
6. ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ መሙላት አለበት፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
9. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ