በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለስማዳ ወረዳ ለፍትህ አካላት የቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚዉል በአልማ እና በመደበኛ በጀት መስታወት፣ ሴራሚክ፣ ዝኮሎ፣ ብረታ ብረት እና የመፀዳጃ ቤት ሳኒተሪ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ህጋዊ /ወቅታዊ/ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስማዳ ወረዳ ግ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ማህተማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም ሥርዝ ድልዝ ፍፁም የተከለከለ ነዉ፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ስ/ወ/ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለዋና ገንዘብ ያዥ ማስያዝና ያስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማቅረብና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 058 667 01 67 ደውሎ ወይም ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 በአካል ጠይቆ መረዳት ይችላሉ፡፡
የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት