ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

በደቡብ ጐንደር ዞን ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ የታች ጋይንት ወረዳ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለከተማው አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሆኖ 1ኛ. የዲች ዘመናዊ የውሃ ማፋሰሻ ግንባታ የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን 2ኛ. የጠጠር መንገድ ጥርጊያ የማሽን ኪራይ ማለትም የዶዘር፣ የኤክስቫተር፣ የግሪደር እና የሲኖትራክ ኪራይ ተከራይቶ ከተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከደረጃ ሰባትና በላይ የሆነ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ግንባታ በማጓተት ወይም በማዘግየት እገዳ ማስጠንቀቂያ ያልተፃበት እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቀረብ የሚችሉ ፈቃዱን ከአወጡ ጀምሮ ግንባታ ገንብተው የማያውቁ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች ከሆኑ ግብር ከሚከፍሉበት ወረዳ ላለመሥራታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የግንባታ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የግንባታ ዓይነት ሁለት በመቶ በባንክ በተርጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፤ ይህም ገንዘብ አሸናፊ ከሆነ ከውል ማስከበሪያ ጋር ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፤ ተሽናፊ ከሆነ ደግሞ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳብ በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታትና በጥንቃቄ በማሸግ ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆይ 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
  10. ጨረታው በ22ኛው በዚሁ ቀን 4፡00 ይዘጋል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፤ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  11. የተሞላው ሰነድ በትክክል የሚነበብ ሆኖ ሥርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት (ሎት) በመሆኑም የተጠየቁትን ዝርዝር አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 268 02 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here