በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስራና ስልጠና ቢሮ ለ2018 በጀት አመት አመታዊ የመኪና መለዋወጫ (እስፔርፓት )በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ1 ዓመት ውል በመያዝ መለዋወጫዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
- አግባብነት ያለው ህጋዊና በዘርፉ የተሰማሩ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የVAT) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር G001 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በማንኛዉም እቃ ግዥ ዋጋ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ለአገልግሎት ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢዉ ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 3 በመቶ የቅድመ ግብር ክፍያ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 ብር 300(ሶስት መቶ ) በመክፈል ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ውድድሩ በተናጠል ስለሆነ ማቅረብ የሚችሏቸውን እቃዎች ብቻ በመለየት መሙላት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛዉ ቀን ማለትም መስከረም 20/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኝዉ ስራና ስልጠና ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ዉስጥ ይከፈታል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ጨረታ ሰነድ ላይ የተሞላውን ዋጋ ማሻሻል መለወጥ ወይም ጨረታዉን ሰርዣለሁ የሚሉት ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡
- ቢሮው ጨረታዉን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 53 97 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ስልጠና ቢሮ