የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት በጤና እና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡የማህበሩ የስቱዲዩ ግንባታ ተጠናቆ የህብረተሰቡን ፍላጐት የሚያሟሉና ውጤታማ የአስተምህሮ ሥራዎችን በመቅረጽ ስቱዲዩውን ወደ ሙሉ አገልግሎት ለማስገባት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የቪዲዬ ካሜራ ከነሙሉ አክሰሰሪው ፣ እስማርት ቴሌቪዥን፣ ኬብል እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር አክሰሰሪዎቹን በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000 ( ሁለት መቶ ሽህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ( ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 /ስድስት መቶ ብር / በመክፈል ባህር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል ፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 7360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር