ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለራሱ አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና ተ/ጽ/ቤቶች ሎት 1. ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ በአንድ ሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም  የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በኦርጅናል በመሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ፣የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወልድያ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ሥር ባሉ ንብረት ክፍል እስቶር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የታዘዙት ጎማና ባትሪ እቃዎችን በታዘዙት የእቃ ዝርዝር መለያ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት መቅረባቸውን በሚያረጋግጥ የገዥ መሥሪያ ቤት ባለሙያ ሲረጋገጥ እርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመሥሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን እቃ ማስረከብ የሚችሉ ፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ፣ስምና ፊርማ፣በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገጹ ማህተም ማድረግ እንዲሁም መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን እንዲሁም ቫት ዊዝሆልድን (7.5%) ታሳቢ ተደርጎ መሞላት አለበት፡፡
  7. ውድድሩ በድምር ዋጋ /በሎት/ መሆኑ ታውቆ በሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይውልና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ቅዳሜና እሁድ ወይም የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የሚከፈት ይሆናል፤ በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ የሞሉትን ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ-1 በመሥሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰብ በማስቆረጥ ኦርጅናሉን በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ስለሆነም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
  13. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ እና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የተሳሳተ ወይም ሥርዝ ድልዝ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፣ በህግም ያስቀጣል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 79 04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • በሎቱ አንድም ሆነ ከአንድ እቃ በላይ ዋጋ ያልሞሉ ተጫራቾች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ ፡፡

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here