ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
131

በአብክመ የፍትሕ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. አላቂና ቋሚ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. አላቂ የጽዳት እቃዎች፣

ሎት 3. ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 4. ቋሚ አላቂ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 5. የኤሌክትሪክ እቃ /ብሬከር/፣ ሎት 6. የውሃ እቃ፣ ሎት 7. የቢሮ ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር የውጭ፣ ሎት 8. የመኪና

ዲኮር፣ ሎት 9. የደንብ ልብስ እና ሎት 10. የብስክሌት ጎማና ካላማዳሪ፣ ጥቅል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወቀረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣታፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ከነቫት ከጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡

10.ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ19/02/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ቢሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

11.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ የህግ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

12.መሥሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 01 31 /058 226 01 22/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፍ/ባ/ማ/የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here