የጎጃም ልማት አክሲዮን ማህበር በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 የድሮዉ የተባበሩት ነዳጅ ማደያ B+G+12 የቅይጥ ህንፃ ግንባታ ሥራ የማማከር አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አጫርቶ ለማሰራት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ማንኛዉም አማካሪ ድርጅት ለታሰበዉ የግንባታ ሥራ ለማማከር ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አማካሪ ድርጅቶች በጨረታዉ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኃል፡፡
- ደረጃ 4 (ደረጃ አራት) እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ፡፡
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላችሁን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢዉ ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ድረስ አክሲዬኑ ቢሮ ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ዉስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ የመወዳደሪያ ሃሳባቸዉን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻቸዉ በታሸገ ኢንቨሎፕ በአክሲዬኑ ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከታተመበት በ10ኛዉ ቀን ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ እንዲሁም ጨረታዉን መታዘብ የሚፈልጉ ማንኛዉም አካል በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፤ የጨረታዉ መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተዉ የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታ ዉጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በኩል በጽሁፍ እንገልፃለን፡፡
- አክሲዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 12 06 47 17 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- በጨረታዉ ለመካፈል ፍላጎት ያላችሁ ይህንኑ የሚገልጽ ደብዳቤ በመያዝ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሞልተዉ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰዉ ቦታ ቀንና ሰዓት መመለስ የሚችሉ፡፡
የጎጃም ልማት አክሲዮን ማህበር