ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
33

የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ላሉት መኪኖች አገልግሎት የሚውል እስፔር ፓርት እንዲሁም የመኪና ጥገና የጉልበት ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማሰራት/ ይፈልጋል፤ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን  መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ  ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸውጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥቅል ዋጋ ለመኪና መለዋወጫ ብር 80,000 (ሰማንያ ሽህ ብር) እና ለመኪና ጥገና የጉልበት ዋጋ ብር 30,000 (ስላሣ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ደግሞ ገንዘቡ በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የዕቃ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የተሸከርካሪ ኮንትራት ጥገና ከሆነ 3 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ፕሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዘዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank grante) ማስያዝ ይኖርበታል፤ ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ከ16 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፤ ተጫራቾች የጨረታ መወዳዳሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት

ለመ/ቤቱ እና ለተጫራቾች ደህንነት እንጂ እንደመወዳሪያ መስፈርት አይሆንም፡፡

  1. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  4. ውድድሩ በሎት ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሱትን ሁሉንም ዝርዝሮች በሙሉ መሙላት ያስፈልጋል፡፡
  5. ለመኪና ጥገና የጉልበት ዋጋ የጋራዦች ደረጃ 2 እና 3 ደረጃ የሚያሟሉ ሆኖ ጥገናው የሚካሄድበት ቦታ ሁለት እጁ እነሴ ድረስ ይሆናል፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጭ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ሥር ባሉ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  7. መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. አሸናፊው ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ የመኪና መለዋወጫውን በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈውን የመኪና መለዋወጫ ሙሉ በሙሉ አጠቃሎ ማቅረብ አለበት፡፡
  9. ለመኪና ጥገና የጉልበት ዋጋ እስከ በጀት አመቱ ማለት ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡
  10. በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here