በሰሜን ወሎ ዞን የወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት 1. ቧንቧ እና መገጣጠሚያ፣ የኤችዲፒ መገጣጠሚያ መፍቻና ጥርስ ማውጫ፣ 2. አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃና የጽዳት እቃዎች፣ 3 ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ 4.የመኪና እቃዎች መለዋወጫ እንዲሁም 5. የኤሌክትሪክ እቃዎች መለዋወጫ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ የሆነ፡፡
- ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጀቱ ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፤ ተጫራቾች ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፤ በቀረቡት እቃዎች ላይ ችግር ቢፈጠር የመመለስ /የመቀየር/ ግዴታ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ በህግ ፊት ይጠየቃሉ፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፋበት የእቃ ዋጋ ድምሩ ከብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- የአሸነፉበት የእቃ ድምር ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች እስከ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት እቃ ድምር ዋጋ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዘው መቅረብ አይፈቀድም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተራ ቁጥር 1, ብር 400፣ ተራ ቁጥር 2 እና 3, በብር 200፣ ተራ ቁጥር 4 እና 5, ብር 300 ብቻ በወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር .1 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
- የሚገዙት የእቃዉን ናሙና /ሳምፕል/ ከድርጅቱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር መመሪያ ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 ጨረታው ይከፈታል፤ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውሃ አገልግሎቱ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 003 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም Email gechmog@gmail.com ፋክስ 033 331 15 72 በስልክ ቁጥር 033 431 12 23 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወልድያ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት