የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት ለሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት፣ ለእነሴ ሳር ምድር ወረዳ ፍ/ቤት እና ለሰዴ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በ2018 ዓ.ም ሎት 1. የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 4, የተለያዩ የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት 5 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 6 የተለያዩ የቢሮ ጥገና ሥራዎች፣ ሎት 7፣ መስተንግዶ፣ ሎት 8 ብትን ጨረቅ እና የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 9 አሽዋና ድንጋይ፣ ሎት 10 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና፣ ሎት 11 ፈርኒቸር እቃዎች እንዲሁም ሎት 12 የተለያዩ የፎቶ ኮፒ ሥራ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ (ቲን) ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከጎ/ሲ/እ/ወ/ፍ/ቤት፣ ከሁ/እ/እ/ወ/ፍ/ቤት፣ ከእነ/ሳ/ም/ወ/ፍ/ቤት፣ ከሴዴ/ወ/ፍ/ቤት፣ ከሁሉም ወረዳዎች ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር 1 /አንድ/ በመቶ ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን ዋና ገንዘብ ያዥ ደረሰኝ በማስቆረጥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ16 ቀናት እስከ 3፡00 ድረስ ክፍት ሁኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡05 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት የድርጅቱን ክብ ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ኦርጅናል ፖስታ በማድረግ በግዥ /ፋ/ን/አስ/ ቡድን በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈጽም ከተገለጸለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከአሸነፉበት የእቃ ወይም የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ጥራት ያለው እቃ በተቀመጠው ሳንፕል /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም ስም ፊርማ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያመጣ /የሞላ ነው፡፡
- ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ፓራፍ ማድረግ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው እንደ አስፈላጊነቱ በጠቅላላ ድምር ውጤት ወይም በሎት በመሆኑ የተጠየቁትን እቃዎች ዝርዝር ሁሉንም አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
- የጨረታው መከፈቻ ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ የሥራ ቀንና ስዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ሁሉንም አይነት እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ወይም የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በ4ቱም ወረዳዎች ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 59፣ 058 664 01 78፤ 058 666 01 38 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ጊዜና ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እና ውል የያዘባቸውን እቃዎች ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍ/ቤት