ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም፡- ሎት 1. አትክልትና ፍራፍሬ  ሎት 2. የዳቦ አቅርቦት ሎት 3. የምግብ ምርቶች ሎት 4. የጽዳት እቃዎች ሎት 5. የቤትና የቢሮ እቃዎች መገልገያዎች ሎት 6. የእህል ወፍጮ አገልግሎት እና ሎት 7.የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም፡-

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
  5. የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ እና ለአግለግሎት ከ10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
  7. የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ መቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸው፤ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር በአንድ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  11. ጨረታው በቀን 04/02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ መኖር የለበትም፤ ነገር ግን ሥርዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  13. ት/ቤቱ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፤ በተጨማሪም ማንኛውም ተጫራች የሚቀርቡ እቃዎችን ሳምፕል ከት/ቤቱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሎት የጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን ምርቱን /እቃውን / በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
  15. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
  16. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
  17. አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ  ግቢ  ወይም 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here