ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ሂደቶችና ለምድብ ችሎቱ  አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎች  ሎት  01 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ፣ሎት 2 ሽሚዝና ጫማ ፣ሎት 03 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 04 የህትመት ዉጤቶች ፣ሎት 05 ነዳጅና ቅባት ፣ ሎት 06 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 07 ሌሎች አላቂ እቃዎች ፣ሎት 08 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ሎት 09 የመኪና ጎማ ፣ሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት 12  የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 12 በአገር ዉስጥ የሚሰሩ ወንበርና ጠረጴዛዎች ፣ሎት 13 የህንፃ መሳሪያዎች እና ሎት 14 የሶፋ ልብስና መጋረጃ ለመግዛት መስፈርቱን አሟልቶዉ ከሚገኙ አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ሥለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ያሳደሱ ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት አያይዘዉ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ፡፡
  2. ግዥዉ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሚፈጸሙ ግዥዎች እና ለኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፤ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 30 (ሰላሳ ብር) ብቻ በመክፈል ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታዉ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ  በታሸገበት ቀን  ከቀኑ 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በግልጽ ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸዉ በቀኑና በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታዉን ከመክፈት አያግድም፤ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. የዕቃ ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ሙሉዉን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር ከሞሉት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን  ቢሮ ቁጥር 5 ከገንዘብ  ያዥ በመ/ሂ1 ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር የደረሠኝ ኮፒ በማሸግ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ዋና ሠነድ በጥንቃቄ  በታሸገ  ፖስታ  በተራ ቁጥር 2 በተገለጸዉ ቦታ ጥቅምት  4 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃዉን መጓጓዣና እንዲሁም ማናቸዉም የመንግስት ታክስን ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፤ ዉድድሩ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  9. ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ካለዎት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም  በስልክ ቁጥር 058 111 44 40  ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here