ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
44

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ እቃ እና የመኪና ጎማ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤቱ ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር ሎት የመኪና መለዋወጫ እቃ ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ሎት 2. የመኪና ጎማ 40,000 (አርባ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማሲያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን፤ ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን የመኪና ዕቃዎችንና ጎማዎችን ወረዳው ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ የሚችልና ለፍትህም ሆነ ለማንኛውም አገልግሎት የሚከፈለውን ወጪ የሚችል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ/ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  15. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፍቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. እቃዎቹን በባለሙያ በማረጋገጥ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  17. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤት ይገልፃል፡፡
  18. አሸናፊው ድርጅቱ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  19. ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  20. ግዥ ፈጻሚው አካል ግዥውን ለመገምጋም ወይም ለማጽደቅ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጀቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት ለ 40 ቀን ይሆናል፡፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 664 04 60 /002 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንቻ አሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here