ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

የግዥ መለያ ቁጥር  አብክመ/ኢቴቢ/ግ/ጨ/ 01 / 2018

በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለተለያዬ አገልግሎት የሚውሉ ሶፍትዌር ሎት 1. አቴንዳንስ ማኔጅመንት ሲስተም ልማት በሀገር ውስጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስለማት ይፈልጋል ፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  3. የሚወዳደሩበት ሎት ግዥ ጥቅል ዋጋ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1 – 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚለሙ ሶፍትዌሮችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በተቋሙ ዋ/ገንዘብ ያዥ ቢ/ቁ/02 በመምጣትና የማይመለስ 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን የሲስተም ልማት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን ፣የንግድ ፈቃድ ሰነድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ  ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል ወይም የዋጋ ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሌላ ፖስታ በማድረግ ለየብቻ በታሸጉ 2 ፖስታዎች (ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት) ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ከመስከረም 26/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ጥቅምት 10 2018 ዓ.ም ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ 8፡30 ጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም ምድብ  ዋጋ  ይሆናል ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች በቴክኒካል ሰነዳቸውና በፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ ፡፡
  13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 68 56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የአብክመ  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here