ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
22

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እና የጽፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከመስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጽፈት መሳሪያ የሚቀርበው በተቀመጠው ናሙና መሰረት ሲሆን አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ውጤት ሆኖም የመኪና መለዋወጫ ዕቃ አሸናፊ የሚለየው በተናጠል ዋጋ ነው እንዲሁም የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኝት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የአሸነፉበትን የመኪና መለዋወጫ እቃ እና የጽፈት መሳሪያ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ባሉት ንብረት ክፍሎች ማድረስ ወይም ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  13. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 ወይም 09 18 73 90 06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም፡፡

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here