በአብክመ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት በግቢዉ ዉስጥ የተጠራቀሙ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና የተለያዩ የተሸከርካሪ ባትሪና ጎማወችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የሚሸጡ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ናሙና የቀረበ ስለሆነ የጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ በማየት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 100,000,00 /አንድ መቶ ሽህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ 26/01/2018 ዓም እስከ 11/02/2018 ዓም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ / ብር በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛዉ ቀን በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ11/02/2018 ዓም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት እንገደዳለን ፡፡
- አሸናፊዉ የሚለየዉ በእያንዳንዱ እቃ ከፍተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግቢ በመገኘት መረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህርዳር ከ/አስ/ መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት