ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
50

በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ /ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሂደት  በወረዳችን ሥር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ከ2018 የመደበኛ በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች  ሊውል የሚችሉ  የጽህፈት መሳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ህትመት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ጀነሬተር፤ የጽዳት እቃ እና የህንፃ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ በጨረታው በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ጨረታው  ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር)  በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ይዘጋና በዕለቱ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም  ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በጽ/ቤቱ የግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ  የጨረታ ማስከበሪያ ለጽ/መሳሪያ 6,000 (ስድስት ሽህ ብር)፤ ለኤሌክትሮኒክስ 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ፤ ለህትመት እና ለጽዳት እቃ ለእያንዳንዱ ብር 1000 (አንድ ሽህ ብር) ፤ ለሌሎች የግዥ ሎቶች ለእያንዳንዱ ሎት 2,500.00 (ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር) በመ/ቤታችን መ/ሂ1 ወይም በባንክ  በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  4. አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፤ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ  በመ/ቤቱ  መሂ/1 ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም  እና አድራሻ በመሙላት የታደሰ ንግድ ፈቃድና  የቲን ምዝገባ ፣የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በማያያዝ  እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ለዚሁ  በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፤ በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  7. በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም ስፔስፊኬሽን መሰረት ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቹ የአሸነፈውን እቃ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሥር በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጐጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ድምር ወይም በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  12. ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 250 04 85 /058 250 00 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደብረ ኤልያስ ወረዳ /ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here