የአብክመ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በስሩ ለሚያስተዳድራቸዉ የገጠር ሽግግር ማዕከላት ሎት 1. ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚዉሉ ባለ ሶስት እግር በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ባጃጆች፣ ሎት 2. preparation of 3d phiscal model for Bure IAIP፣ ሎት 3. የግብርና ዕቃዎች /ግሪነሪ መሳሪያዎች/ እና ሎት 4. ለፓምፕና ጀኔሬተር ጥገና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ገንዘብ ያዥ ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአረጋዊያን ህንጻ ከሚገኘዉ ኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የካሌንደር ቀናት ዉስጥ እስከ 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፤ ነገር ግን በ21ኛዉ ቀን ወይም በመዝጊዉ ቀን የጨረታ ሰነድ አይሸጥም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት እስከ 21ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ሲኖርባቸዉ፤ 21ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የመክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 09 ዉስጥ በ21ኛዉ ቀን 4፡00 ይታሸግና በዚያዉ ዕለት 4፡30 ይከፈታል፤ ሆኖም 21ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ይታሸግና በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ዋጋ ይሆናል፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎችን ባሕር ዳር በኮርፖሬሽኑ ቢሮ ድረስ በማምጣት ማስፈተሸ /በባለሙያ ማሳየት/ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኢፓልኮ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 47 67 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን