ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
140

በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፍል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. /የቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

3. ለተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርትፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ ነጥብ አምስት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ እና በመሥሪያ ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ- 1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ጨረታው በአየር ላይ ከ 04/02/2017 ዓ/ም እስከ 18/02/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ04/02/2017 እስከ 18/02/2017 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 19/02/2017 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ 9፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡

11. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡

12. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡

13. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡

14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታችው በባለሙያ እየተረጋገጠ ማ/ጎንደር ዞን ከሻጭ መጋዝን ነው፡፡

16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 10 በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ. 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here