በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1.የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ ሎት 2. የመኪና ጎማና ባትሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ እና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1.5 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመስከረም 26 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከመስከረም 26 ቀን 2018 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም 8፡00 ታሽጎ 8፡15 ይከፈታል፤ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት ፅንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ እየተረጋገጠ ማ/ጎንደር ዞን ከሻጭ መጋዝን ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት