በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ለሚፈፀማቸዉ በመደበኛ በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 ቋሚ እቃ ሎት 5 ህትመት እንዲሁም ሎት 6 የችሎት ካባ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፤ ስለዚህ በዘርፍ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ማንኛዉም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዘጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ እስከ 60 /ስልሳ/ ቀን ያላነሰ የሆነ የሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ /ሲፒኦ/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥ ቡድን ወይም በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሁሉም ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ወይም በነጠላ አሸናፊው ለሚሆነው ነው፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳማና እሁድ እንዲሁም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ በእያንዳንዱ ግዥ ላይ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን የሚያስረክበው በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመ/ቤቱ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በሥልክ ቁጥር 033 114 02 83 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በፖስታው ላይ ቀን፣ ሥም፣ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር የሚወዳደሩበት ዘርፍ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 (ሃያ ብር) በመክፈል ለጋምቦ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የለጋምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት