ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
34

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የደራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ያሉ 4ቱም ፑል መሥሪያ ቤቶች ያለ አገልግሎት የተቀመጡ እና የአገልግለት ጊዜያቸዉ ያበቃ ብረታብረቶች፤ ቁርጥራጭ የተሸከርካሪ እና የማሽነሪ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ከ1-3 ለተዘረዘሩት ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  6. የሚሸጡ ብረታ ብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብረታ ብረት ብር 100,000 /አንድ መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን በማሸግ ከፖስታው ጀርባ ለደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በማለት ዘወትር በሥራ ሰዓት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎትም ሆነ በተናጠል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 71 69 38 /09 13 93 62 60 /09 77 96 82 68 ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here