ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
51

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ ዕቃ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ሎካል ፈርኒቸር፣ ሎት 4 የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ኢምፖርትድ ፈርኒቸር እንዲሁም ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እያንዳንዱን ሎት በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላቸችሁ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው የአገልግሎቱ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን ሎት በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም የዕቃውን አገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ ዕቃ ብር 5,000 ፤ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ብር 1,000 ፤ ሎት 3 የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ሎካል ፈርኒቸር ብር 10,000 ፣ሎት 4 የቤትና የቢሮ ዕቃዋች ኢምፖርትድ ፈርኒቸር ብር 5,000 እንዲሁም ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 10,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ህጋዊ ደረሰኝ መሂ-1 ተቆርጦ ኮፒውን ከሠነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ፋይ /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. እንደ በጀቱ አቅም 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በሟሟላት ከያንዳንዱ በሎት ድምር ዝቅጸተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ሠዓት ይከፈታል፡
  13. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 ሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ አዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖርበታል፤ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኋላ የአሸነፋቸውን ዕቃዎች አዲስ ቅዳም ከተማ ድረስ አጓጉዞ ያደርሳል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 450 06 54 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዲስ ቅዳም ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here