በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት በወረዳው ላሉ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚዉሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመኪና ጎማ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ከማዕላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ሂ 1 በመክፈል ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነና ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በጥቅምት 18/2018 ዓ.ም 3፡00 ይዘጋና 3፡00 ቢሮ ቁጥር 05 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻው በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እና በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት