ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተሽከርካሪዎች እና የአሽከርካሪዎች እንዲሁም 3ኛ ወገን የመድን ኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የአገልግሎት ዋጋው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የተሽከርካሪዎች እና የአሽከርካሪዎች እንዲሁም 3ኛ ወገን የመድን ዋስትና አገልግሎት ግዥ እና መኪኖች (ተሸከርካርዎች) ላይ የሚገጠም ጅፒኤስ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የተሽከርካሪዎች እና የአሽከርካሪዎች እንዲሁም 3ኛ ወገን የመድን ዋስትና አገልግሎት ግዥ ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብ/ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Garntee) ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮሚሽኑ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ  ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች አንዱን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
  12. አንድ ተጫራች በወጣው ጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መ/ቤት በጽሑፍ ወይም በፋክስ ማቅረብ ይችላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መ/ቤትም ለተጠየቀው ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሑፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  15. የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባሕር ዳር ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 218 00 14 /058 218 11 03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here