ቁጥር KFW/ግ/1/2018
የአብክመ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለደቡብ ወሎ ብዝሃህይወትና ደን ልማት ፕሮጀክት (KFW) ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ቁጥር፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑትን አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የደንብ ልብስ፣ ስማርት ሞባይል ቀፎና የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ሠነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋንቢ ጎን ካለው የአካ/ጥ/ባለስልጣን መ/ቤት አዲሱ ህንፃ ግራውንድ ላይ ግዥ ቢሮ በመምጣት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የጨረታው ሠነድ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ቀን 3፡00 ድረስ ግዥ ቢሮ አጠገብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጨረታ መዝጊያው ቀን 3፡01 ታሽጐ 3፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን በመ/ቤቱ ግዥ ቢሮ ይከፈታል፤ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠ/ዋጋ አንድ በመቶ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸውል፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ሥም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ከ20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ለሆኑ ግዥዎች ቫቱን በግማሽ በመቶ ቢሮው የሚያስቀር መሆኑን አናሳውቃለን፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት በነጠላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 62 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ አካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለስልጣን
ባህር ዳር