ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማና ዲኮር እና የህትመት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ግብር) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 9 ሰነዱን በመግዛት የእቃዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ የተቀመጠውን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ግቢ ውስጥ በግዥ ፋይናንስ አስተዳደር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3፡00 ይታሸግና 3፡30 ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ አብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 38 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ቀበሌ 13 ሆምላንድ ሆቴል አካባቢ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክቡራና ገብርኤል ቅርንጫፍ ፊትለፊት

የአብክመ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here