ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
13

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አይቬኮ የዉሃ ቦቴ አጠቃላይ የቦዲ የመካኒካልና የኤሌክትሪካል ሲስተም  የጥገና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኤጀንሲዉ ሥም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ደረሰኝ በማስቆረጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሥም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፤ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው አንድ በመቶ ከብር 500,000 /ከአምስት መቶ ሽህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሽህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጥቅምት 10/2018 ጀምሮ እስከ ቀን ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማዉረጃ ወጭን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ በቀን ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ግዥ ኢፊሰር ቢሮ በ08፡30 ኤጀንሲዉ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት፣በፖስታ ቁጥር 382 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 11 15 /058 320 77 69 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው፤ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

የአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here