የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለምግብነት የሚውሉ ንፁህ በቆሎ ብዛቱ 17,160.80 የሆነ፣ ያልተበጠረ ጤፍ እና የተለያዩ ብጣሪዎችን ለመሸጥ እንዲሁም አዲስ የዘር ማሽጊያ ክረጢት ለማሳተም፤ ጥራቱን ጠብቆ ሊያጭድና ሊወቃ የሚችል የኮምባይን ሀርቨስተር ለመከራየት እና ከወረዳዎች የተመረተዉን ዘር በአራቱም ጣቢያዎች ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚሀ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (ቲን) ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ሥምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርፕራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፤ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
- ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
- ያገለገለ ጆንያዎችና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርብ አይገደድም፡፡
- ግዥዉን በተመለከተ ባሕር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዝን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀው ውስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን እስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 /09 18 01 69 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ