በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሎት 1 ለከሚሴ እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ግንባታ የኮርኒስ ሥራ የሚሆን የአርምስትሮንግ አቅርቦትና ገጠማ ሥራ፣ ሎት 2 ለወልድያ አያሙሌ ቤተ-መጻሕፍት ግንባታ የኮርኒስ ሥራ የሚሆን የአርምስትሮንግ አቅርቦትና ገጠማ ሥራ፣ ሎት 3 ለከሚሴ እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ግንባታ 75ሜ3 GRP የውሃ ታንከር አቅርቦትና ገጠማ ሥራ በዘርፉ በተሰማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በፊት በዘርፉ የሰሩበትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም አብረው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) የባንክ ጋራንቲ ዋና (ኦርጅናል) ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ ተቀባይነትም የለውም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ወልዲያ ከተማ በሚገኘው ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 4:30 ላይ ታሽጎ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ሰዓት ማለትም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፣ የጨረታ አሸናፊም በእያንዳንዱ ሎት ሳምፕል በማቅረብ የቀረበውም ሳምፕል በአማካሪ በኩል መጽደቁ ተረጋግጦ የአቅርቦትና የገጠማ ሥራው በራስ ወጭ ሳይት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ክፍያን በተመለከተ በሁሉም ሎቶች በአማካሪዎች በጸደቀው ሳምፕል መሰረት ቦታው ድረስ ማቅረብና መግጠም ሲችሉ ነው፡፡
- በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
- ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ብቻ መሙላት አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ