በምሥራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ ስፒር ፓርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰዉን እና የሚመለከተውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሎት 1 ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር ለሎት 1 ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጀዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ አለበት ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እን፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማፅደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስገሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት