ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉና ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የሰራተኞች የደንብ ልብስ ብትን ጨርቆች፣ የተዘጋጁ ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ቆዳ ጫማ፣ የወንድ የፕላስቲክ ቦት ጫማ እና ልዩ ልዩ አልባሳት ፣ ሎት 2 የጽዳት መገልገያና

ጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የውሃ ጥራት፣ ሎት 4 የቢሮ መገልገያዎች፣ ሎት 5 ኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች፣ ሎት 6 ሜካኒካል ቱልስ፣ ሎት 7 ሰርፌስ ፖምን እንዲሁም ሎት 8 ቧንቧና መገጣጠሚያ  አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙበትን የዕቃዎች የጠቀሜታ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ናሙና ወይም ብሮሸረ ለሚያስፈልጋቸው አቃዎች ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዘውትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካሉን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ፋይናንሻሉን ሲፒኦውን ጨምሮ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ለየብቻ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታ ሰነዱን 4፡00 ድረስ በማስገባት ከረፋዱ 4፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡
  8. ለተጨማሪ ማብራሪያ ኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስልክ ቁጥር 033 351 02 72 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here