ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
18

የጨረታ ቁጥር ፡ 001/ ፊ/የሀ/ግዥ/2018 ዓ.ም

በምዕራብ ጐጃም ዞን ለፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር ለፋብሪካዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 01 የጽህፈት እቃዎች፣ ሎት 02 የጽዳት እቃዎችን እና ሎት 03 የኮንስትራክሽን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱና በናሙና የቀረቡትን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት 2፡00 እስከ 6፡00 እና ከስዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 እና ከስዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት እና በ16 ተኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተወደዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም የሚከፈትበት ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሀገር ዉስጥ ግዥ ዋና የሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 09 10 69 31 95 /09 13 60 61 13 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ፊቤላ ኢንዱስትሪያ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here