ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
9

በቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ንአስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ለይቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የመኪና ጎማ፣ ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የመናህሪያ በር ግንባታ ስለሆነም ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሚመለከታችሁ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግዥው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚፈለገውን የእቃ አይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመሂ 1 የተቆረጠ ጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ከጥቅምት 10/2018 እስከ ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በቀን ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሽጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም 4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ወይም በስልክ ቁጥር 058 271 00 31 /0269 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. የመክፈቻ ቀን (ሎት 1 የመኪና ጎማ ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  2. ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ እቃ ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
  3. ሎት 3 መናሃሪያ በር ግንባታ ህዳር 01/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  4. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
  5. እቃውን የምንረክበው በያዝነው የበጀት ልክ ነው፡፡
  6. ከላይ ደረጃ 9 ተበሎ የተለየ ለመናሃሪያ በግንባታ ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የግንባታ ጨረው 21 ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡

የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here