ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
10

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ/ም በወረዳው ውስጥ የሚገኙ አገልግሎት ሰጥተው የተመለሱ እና በስራ ላይ እያሉ የተበላሹ አሮጌ ብረታ ብረቶችን ማሽነሪዋችን የአልሙኒየም ውጤቶችን እና መሰል እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደር መብት አለው፡፡
  2. ጨረታው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) አይጠይቅም፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ቀን ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣትና ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጉልህ በተፃፈ አድራሻ ምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖረባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ምዕራብ በለሳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከረዳት ገንዘብ ያዥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ከሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆነው አካል (ድርጅት) ያሸነፉበትን አጠቃለይ እቃ በእራሱ ትራንስፖርት ማስጫኛና ማውረጃ እንዲሁም የሚዛን ኪራይን ጨምሮ በእራሱ ወጭ የሚሸፍን መሆን አለበት፡፡
  7. አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በተራ ቁጥር 5 በተገለፀው ተቋም ማስያዝ አለበት፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከፊት ለፊቱ ልዩ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ፖስታው ላይም ሆነ ከጨረታ ሰነዱ ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም፣ ስልክ ቁጥር እና ሙሉ አድራሻውን መፃፍ ይኖርበታል፡፡
  11. ይህ ጨረታ በክልሉ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር መመሪያ የሚተዳደር ይሆናል፡፡
  12. ጨረታው ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 70 11 12 04 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here