በሰሜን ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የአዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ለአዴት ከተማ አስተዳደር ለመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የእቃዉን ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ወጥቶ ይቆያል ሰነዱን በአዴት ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት በግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠት (ቢድ ቦንድ) ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤችን ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ሰነድን ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የዋጋ መሙያ ፎርሙን በመሙላት በፖስታ በማሸግ በአዴት ከተማ አስ/ገን/ ጽ/ቤት በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16 ተኛው ቀን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፤ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ቢኖረውና ለመለየት አስቸጋሪ ከሆነ ተጫራቹ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ እቃ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር በሎት ይሆናል፤ ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት አይቻልም፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆኑ በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ /ባለሙያ/ ተረጋግጦ የምንረከብ መሆኑንና ልዮ ሙያ የሚጠይቅ ከሆነ በቴክኒካል ባለሙያዎች የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 338 00 43 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለዉ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
ማሣሰቢያ፡- እኛ ከሸጥንላችሁ ሰነድ ውጭ በራሣችሁ ቅጽ መሙላት፣ በፍሉድ ማጥፋት፣ ሥርዝ ድልዝ፣ በራስ ስፔስፊኬሽን ዋጋ መሙላት፣ ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት እና የድርጅት ማህተም ያላደረገ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
የአዴት ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት