በደቡብ ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን በ2018 በመደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳርያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ እንዲሁም ሎት 6 ህትመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን፣ በድርጅቱ ስም፣ የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ ስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ይውላል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል፤ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታውን ለመክፈት ቢገኙም ባይገኙም አያስተጓጉልም፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደርያ ሃሳብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 09 32 82 45 54 ደውሎ መረጃ በመጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት