ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
8

በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ የሚገኘው ርብ ኃላ/የተወሠነ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ቀበሌ 04 በመደበኛ በጀት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ባለቢዝመንት ሦስተኛ ፎቅ (B+G+3) ለማሰራት  ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለሲሚንቶ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. አቅራቢዎች ህጋዊና በዘመኑ የታደሠ የንግድ የስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የወጣው ጨረታ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ እንደሚሆን ሲገመት የተጨማሪ የእሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ በአማረኛ ቋንቋ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች በሚሞሉበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸው እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ከተማ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ለ10 ተከታታይ ቀናት የመጫረቻ ሠነዱን ዋናው ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በአካል (በህጋዊ ወኪላቸው) በኩል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  8. የሲሚንቶ የሚቅረቢያ ቦታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፡፡
  9. የመጫረቻ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን 10 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. የመጫረቻ ሰነዱ በ11ኛ ቀን ከረፋዱ 5፡30 ተዘግቶ በዕለቱ 6፡00 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎች) በተገኙበት ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ሰነዱ በአንድ በጥንቃቂ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦሪጅናል ሰነዱ ፖስታ ውሥጥ በማደረግ መቅረብ አለበት፡፡
  12. ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የሲሚንቶ አቀራረብ ሁኔታ በተመለከተ በተጫራቾች መመሪያ ይመልከቱ፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  15. ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችን በስልክ ቁጥር 058 444 00 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ርብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here