ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
25

በምሥራቅ ጐጃም አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአነደድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ማለትም፡- ሎት 1 ደን ዘር፣ ሎት 2 የቡና ፕላስቲክ፣   ሎት 3  አሽዋ፣ ሎት 4 ጆንያ፣ ሎት 5 የችግኝ ጣቢያ ቁሳቁስ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን አስታውቋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከአነ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን (ቢድ ቦንድ) በአንድ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ አድራሻና ፊርማ በመሙላት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በአነደድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጫረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሰሳይ ሰዓትና ቦታ ታሽጎ በዚያው እለት ከከረፋዱ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ የጨረታ ሳጥኑን ሲከፈት ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታውን ከመክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት የአሸነፈበትን እቃ (ንብረት) ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ውል ማስከበሪያ  ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የአሸነፉትን እቃ (ንብረት) ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል ሲሆን አሽዋውን በተመለከተ ደግሞ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ላይ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ አሸንፎ ሲመጣ ዉል ለመያዝ የሚያስፈልጉ ወጭዎችን መሸፈን ይኖርበታል፡፡
  11. ዉድድሩ በጥቅል ዋጋ (በሎት) ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አነደድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት የግብርና ግብ/ ገጠ/ፋይ/አገ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 261 00 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአነደድ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here