ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
7

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ከ የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማቴሪያል ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከጥቅምት 17/2018 ዓ/ም ጀምሮ የምሥራቅ ደምበያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የግንባታ ማቴሪያል ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ጥቅምት 17/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 1/2018 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ህዳር 01/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ በግዥ ግን/አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 በዚሁ ቀን ህዳር 1/2018 ዓ/ም በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኝም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባው ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታውን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለው፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው እና የውል ስምምነት እንዲፈጽሙ በተገለጸበት ጊዜ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ እና ንብረቱን ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ አስተዳደር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግና የጫኝና አውራጅ በተጫራቾች የሚሸፈን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 90 06 /058 335 06 01 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here