የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልገሎት የሚውል በመደበኛ በጀት ሎት 1 ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ስፔር ፓርት)፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ አቃዎች፣ 5 ሎት መኪና ዘይት እና ቅባት ሎት 6 የኮምፒውተር ወረቀት፣ ሎት 7 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅ ዋጋ እና ሎት 8 ልዩ ልዩ የኮምፒውተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቀጥር (ቲን) ያላቸው፤ ግዥው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ሎት 1 ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ አቃዎች (ስፔር ፓርት)፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 የመኪና ዘይት እና ቅባት ሎት 6 የኮምፒውተር ወረቀት ሎት 7 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅ ዋጋ፣ ሎት 8 ልዩ ልዩ የኮምፒወተር ቀለም ዝርዝር መግስጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንከ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመሂ1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ዋጋ አንድ በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዥውን ዋጋ ገቢ በማደረግ ከፖስታው ውስጥ በማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅጽ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ስዓት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፤ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ዓመታዊ ውል ስለሚሆን የጨረታውን ዋጋ ጸንቶ ከሚቀይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል አስኪቋረጥ ድረስ ለ20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናውን አና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ጨረታውን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየሎቱ በጥቅል ሰለሆነ የሙሉ ዕቃ ዋጋ መሞላት አለበት፤ ካልተሟላ ግን ከጨረታው ውጭ የሚሆን መሆኑን አንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መወሰድ የሚችልና ዕቃዎችን መተማ ወረዳ ንብረት ክፍል በዝርዝር ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ዕቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጂ ሥርዝ /ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሰባሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማሰከበሪያ የሞላውን ጠቅላሳ ዋጋ 10 በመቶ (ሲፒኦ) በማስያዝ በወረዳው አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት ፡፡
- ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያ ጨረታ በተመለከተ ዕቃው ወደ ንብረት ክፍል በዝርዝር ገቢ ከመደረጉ በፊት ኦርጅናል መሆን አለመሆኑን በሚመለከተዉ ባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ወደ ንብረት ክፍል ዕቃዉ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ጊዜያዊ የሚል ንግድ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ሰርተፊኬት ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወደም በስልክ ቁጥር 058 331 02 68 /058 331 00 17 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

