የባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የፅሕፈት መሳሪያ እና የፅዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ጨረታው ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የማይመለስ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ሲሞሉ በፖስተው ላይም ሆነ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን በሚሞሉበት ጊዜ በጨረታ ዋጋው ማቅረቢያ ላይ ምንም አይነት በነጠላም ሆነ በጥቅል ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ጨረታውን በሚሞላበት ጊዜ በተጠየቀው መለኪያ መሰረት መሙላት አለበት፡፡
- እያንዳንዳቸውን እቃ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ/ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ3ወር የሚቆይ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወደደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በኮሌጁ ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ በጥቃቅን የሚወዳደሩ ከሆነ ከኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀናት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ ጨረታውን በጥቅልም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ንብረቱን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ በሙያተኛ በማረጋገጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 218 05 74 እና ፋክስ ቁጥር 058 218 05 78 መደወል ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

