ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
5

በላይ አርማጭሆ ወረዳ የልማት በር መሰናዶ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚሰጡ ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የ2017 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች በወረዳው የላይ አርማጭሆ ወረዳ ልማት በር ከፍ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ከገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ዋናውንና ቅጂው ተለይቶ በ2 ኮፕ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ስ15 ቀናት ሰነዱን በወረዳው የላይ አርማጭሆ ወረዳ ልማት በር ከፍ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ገንዘብ አንድ በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በጨረታ መክፈቻ ዕለት በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከሆነ ፀንቶ መቆያ ጊዜው ዘጠና ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤ የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ካለበት እና ስለመሰረዙ ልዩ ፊርማ ከሌለበት ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ዋጋ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
  11. አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ከት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት አለበት፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች ኦሪጂናል ያልሆነ እቃ ቢያቀርብ ውሉ የሚሰረዝ መሆኑ አና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
  13. ጨረታው ሙሉ ወጪውን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  14. አሸናፊው አካል በፍትህ ውል የሚወስድ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  1. ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥራችን 09 18 80 57 58 ወይም 058 116 07 18 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡

ማሳሰቢያ፡- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የልማት በር መሰናዶ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here