ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
5

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትሳተፉ ይጋበዛል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ሻት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጣቁሳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 15 ቀናት 11፡30 ተሽጦ በ15 ተኛው ቀን 3፡30 ይታሸጋል፡፡
  7. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣ በ16 ተኛው ቀን በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጣቁሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽ/ቤት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታዉ አይስተጓጎልም፡፡
  8. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፈው የሚለየው በሎት (በጥቅል) ዋጋ ነዉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ ጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለበት፤ የአሸነፈዉን ንብረትም ጣቁሳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ ማስረከብ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 336 04 48 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here