ቁጥር 6/2018
የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚስጡ ሎት1. ተመልካቾችን እያዝናና የሚያስተምር ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ፣ሎት.2 የቴሌቪዥን ሲትኮም ፣ሎት3. ለአማራ ራዲዮ እና ለአማራ ኤፍ ኤም ባ/ዳር 96.9 ተከታታይ ድራማ የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት መረጃ የሚያቀርቡ፣ ከጨረታ ስነድ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነታቸውን የሚያረጋግጥ የቫት ሰርተፍኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ባህር ዳር አማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ግዥ/ን/ጠ/አ/ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ 500 /አምስት መቶ ብር / መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን በመሙላት በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ/ን/ጠ/አገ/ዳሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት (ስፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ጨረታው የፋይናንሻል እና የቴክኒካል (ፕሮፓዛል) ሰነዶች ለየብቻ በፖስታ ታሽገው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ድርጅቶች ሰነዱ ጋር ተይዞ በቀረበው የቴሌቪዥን ድራማና ሲቲኮም እና የሬዲዮ ድራማ አይነትና ጥራት መሰረት ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፓሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ በሚወስደው አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

